ማስታወቂያ:Orignal Certeficate /ቋሚ ሰርተፍኬት/ለምትወስዱ
 • የወሰዳችሁትን የጊዜያዊ ሰርተፍኬት 1 ፎቶ ኮፒ
 • 3x4 የሆነ 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ /ሁለት ጆሮ የሚያሳይ መሆን አለበት/
 • የአገልግሎት ክፍያ 20 ብር
 • ቀጠሮ የሚያሲዙት ጊዚያዊ ሰርተፍኬት ከወሰዱበት ቅ/ፅ/ቤት ነው
 • ቋሚ ሰርተፍኬቱን የሚወስዱት ጊዚያዊ ሰርተፍኬቱን ከወሰዱበት ቅ/ፅ/ቤት በቀጠሮ ቀን ይሆናል፡፡
 • ለሙያ ብቃት ምዘና ተመዝጋቢዎች በሙሉ
 • 1. በትምህርት ማስረጃ የሚመዘገቡ ከሆነ
 • ዲፕሎማ/ሌቭል/ሰርተፍኬት ዋናውን ከፎቶኮፒ ጋር
 • መጠኑ 3X4 የሆነ 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ/ሲመዘገቡ በካሜራ ሊነሱ ይችላሉ
 • ትክክለኛ የምዝና ክፍያ ደረሰኝ ከንግድ ባንክ ይዞ መምጣት
 • 2. በልምድ ብቻ ለምትመዘገቡ
 • የሥራ ልምድ ማስረጃ ሁለት ዓመትና በላይ
 • መጠኑ 3X4 የሆነ 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ/ሲመዘገቡ በካሜራ ሊነሱ ይችላሉ
 • ትክክለኛ የምዝና ክፍያ ደረሰኝ ከንግድ ባንክ ይዞ መምጣት
 • ደንበኞች ወደ ምዝገባ ክፍል ሲመጡ ማሟላት ያለበቸው
 • ከመረጃ መስጫ ክፍል የተሰጦትን ቅፅ በአግባቡ መሙላት
 • የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝ ከሞሉት ቅፅ ጋር አብሮ ማቅረብ
 • ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ተቋማት የሰልጣኞችን መረጃ በፎርማቱ መሰረት በሶፍት ኮፒ መያዝና
 • የምዘና ክፍያ በጋራ ማስገባትና የባንክ ደረሰኝ መያዝ እንዲሁም ፎቶቸውን በሶፍት ኮፒ ይዞ መምጣት
 
የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አድራሻ
 • የምስራቅ አ.አ ቅርጫፍ ጽ/ቤት
 • አድርሻ፡- መገናኛ ገነት ኮሜርሺያል ህንጻ 3ኛ ፎቅ
 • /*
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡10000149325771-ኢትየጵያ ንግድ ባንክ
 • */
 • ስልክ ቁጥር፡- 0116673548
 • የምዕራብ አ.አ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
 • /*
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡-1000148286314-ኢትየጵያ ንግድ ባንክ
 • */
 • አድርሻ፡- ልደታ ቤተክርስትያን አጠገብ
 • ስልክ ቁጥር፡- 0115573245
 • የደቡብ አ.አ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
 • /*
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡-1000149473509-ኢትየጵያ ንግድ ባንክ
 • */
 • አድርሻ፡- አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት
 • ስልክ ቁጥር፡- 011-8-70465/0118704680
 • የሰሜን አ.አ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
 • አድርሻ፡- ሰሜን ሆቴል ፊትለፊት ዳኪ ህንጻ 1ኛ እና 2ኛፎቅ
 • /*
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡-100161890627 -ኢትየጵያ ንግድ ባንክ
 • */
 • ስልክ ቁጥር፡- 011-2-733405/0112733987
 • የማዕከላዊ አ.አ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
 • አድርሻ፡- አራት ኪሎ ቀዳማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ጎን ኤልሳ
 • /*
 • የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡-1000161890627-ኢትየጵያ ንግድ ባንክ
 • */
 • ስልክ ቁጥር፡- 0118120490
 • ማሳሰቢያ ፡ ከላይ የተጠቀሰውን አካውንት ቁጥርና የሚመዘገቡበትን ቅርንጫፍ በትክክል በመለየት የሚመዘኑበትን የሙያ ዓይነት ክፍያ ከዌብሳይት ላይ በማየት
 • በየትኛውም የኢትየጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ይዘው በቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመሄድ ይመዝገቡ!
 • ለአዲስ ተመዝጋቢዎች በሁሉም ሙያዎች በየቀኑ በስራ ሰዓት ምዝገባ እየተካሄደ ነው!
 • ለሰው መመዝገብ በፍጹም የማይቻል መሆኑን እንገልጻለን !
 • የሙያ ምዝና የሚጀምረው ከታችኛው ሌቭል ነው!!
 • REGISTRED NOW! ASSESED! CERTEFIED!


 • የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር መልዕክት

  :

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል አገራችን በ2017 መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ በኢንዱስትሪው የሚመራ ጥራት ያለው የምዘና ሂደቱን በጥናትና ምርምር የተደገፈ በማድረግ የዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማስፈን የአገልግሎት ተጠቃሚ ህዝብ እርካታ እንዲያገኝ በማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ሙያተኛ ለኢንዱስትሪው ለማቅረብ በቁርጠኝነት መልካም ስነ-ምግባር በመላበስ ለህዝባችን በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት ተግተን እንሰራለን፡

                                            ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል


    ዋና ዳይሬክተር

  የማዕከሉ

  :

     ራዕይ

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢንዱስትሪው የሚመራ ጥራት ያለው የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓትን በማስፈን በ2017 ብቃቱ በምዘና የተረጋገጠ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደሪ የሆነ ብቁ ሙያተኛ ወደ ኢንዱስትሪው ገብቶ ማየት::

      ተልዕኮ

  ኢንዱስትሪውን መሪ በማድረግ በምዘና መሳሪያዎች ዝግጅት መዛኞችን በማፍራት፣በምዘና ማዕከልነት በማሳተፍ በምርምርና በመረጃ የታገዘ የምዘና ስርዓት በማስፈን በስልጠናም ሆነ በልምድ የሙያ ባለቤት የሆኑ ባለሙያዎችን በምዘና ብቃታቸዉን በጥራት ማረጋገጥ ነዉ፡፡

     እሴቶች:
 • o ግልፅነት
 • o ቅንነት
 • o ፍትሃዊነት
 • o ተጠያቂነት
 • o ለለውጥ ዝግጁነት
 • o የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • o በጥናትና ምርምር መመራት
 • o በእውቀትና በእምነት መስራት
 • o ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት
 • o ለህዝብ ተጠቃሚነት እንተጋለን
 •  Core Values:
 • Quality
 • Professional ethics
 • Accountability
 • Transparency
 • Best service
 • We are governed by knowledge and skill
 • We are working for the benefit of the nation


 • Latest News :

  ማዕከሉ ከመዛኞች ጋር ውይይት አካሄደ


  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በምዘና ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችና በኮምፒውተር የታገዘ የንድፈ ሃሳብ ምዘና አሰጣጥ ዙሪያ ከመዛኞች ጋር በቀን 24/03/2011 ዓ.ም በራስ አምባ ሆቴል የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡


  በዕለቱ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የምዘና ዝግጅትና አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ አመንቴ ሲናገሩ የሙያ ብቃት ምዘና ዋና አላማው ብቃቱ የተረጋገጠና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለኢንደስትሪው ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡ዲጂታል (በኮምፒውተር የታገዘ) ምዘና የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ የሚያደርግ ሚስጥራዊነቱንና አስተማማኝነትን የሚፈጥር የምዘና ስርዓቱን ለማዘመን የሚጠቅም ነው ብለዋል፡፡በተጨማሪም በምዘና ስርዓቱ የሚታዩ ችግሮችን ሲገልጹ በመዛኞች በኩል ፓኬጅ ይዞ ለመሄድ መሞከር ፣አድልዎ መስራትና ስልጠና እንሰጣለን ማለት የሚጠቀሱ ሲሆን በተመዛኞች በኩል ኩረጃ መፈለግ ፣ምዘናን ያማከለ ስልጠና መፈለግ፣መዛኞችን በጥቅማጥቅም ለመደለል መሞከርና ተያያዥ ችግሮች እንደሚታዩ አንስተዋል፡፡
  በማዕከሉ በኩል የሚታዩ ችግሮች ፍትሃዊ ያልሆነ የመዛኝ ምደባ ፣የመዛኝ ክፍያ መዘግየት፣ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች እንደሚታዩ አንስተዋል፡፡
  መዛኞች በቀረበው ሰነድ ላይ ሀሳባቸውን ሲሰጡ የንድ-ፈሀሳብ ምዘናው በኮምፒውተር የታገዘ መሆኑን አድንቀው ፓኬጆች በተመዛኞች እጅ እንደገቡ፣ የምዘና ጣቢያዎች የግብዓት እጥረት ፣ተመዛኞች ስለ ኮምፒውተር ያላቸው እውቀት አነስተኛ መሆንና የመሳሰሉትን አንስተዋል፡፡

  የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በተነሱ ጉዳዮች ላይ መልስ ሲሰጡ የተነሱት ችግሮች መኖራቸውን ገልጸው ችግሮችን ለመፍታት ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግና ለተቋሙ ድክመትም ሆነ ጥንካሬ የመዛኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ችግሮችን የአጭርና ረጂም ጊዜ ብሎ በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ የመዛኞች ድጋፍ ሲታከልበትና የቴክ ኖሎጂ አጠቃቀማችን ሲሻሻል ተቋሙን የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡


  Return to Top


  Latest News:

  ከኢንደስትሪው ለተመለመሉ ባለሙያዎች የመዛኝነት ስነ-ዘዴ ስልጠና ተሰጠ፡፡


  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ሃምሳ ስምንት ለሚሆኑ ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች የመዛኝነት ስነ-ዘዴ ስልጠና ከህዳር 3/2011 እስከ ህዳር 7/2011 ለአምስት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡


  አቶ አበራ አመንቴ የምዘና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የስልጠናው አስተባባሪ እንደገለጹት ከሆነ አገራችን የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል ወሳኝ በመሆኑና ባለሙያውም በምዘና ስርአት ማለፉ የበቃ የሰው ሃይልን ለማግኘት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ባለሙያዎቹ ከስምንቱ የትኩረት ዘርፍ ሞያዎች ማለትም ከቴክስታይልና ጋርመንት፣ከብረታብረት፣ከባህል ስፖርትና ቱሪዝም፣ ከንግድ፣ ከጤና፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከአይሲቲ፣ ማኑፋክቸሬንግ ኢንደስትሪዎች የተውጣጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

  ለእጩ መዛኞች ስልጠና እየተሰጠ

   

  የምዘና ስነ-ዘዴ የወሰዱ ባለሙያዎች በሙያቸው ሶስት አመትና በላይ የሰሩ እንደየሙያቸው ሁኔታ የትምህረት ደረጃቸው ዲፕሎማ ፣ዲግሪ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ናቸው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ከመጀመሪያው ደረጃ ጀምሮ ምዘና ወስደው ብቃታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ አመላመላቸውም በዋናው ቢሮና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ በማስገባት የተመረጡና የመጡበት ኢንደስትሪም ስለመልካም ባህሪያቸው አምኖ የመሰከረላቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

      

  እጩ መዛኞች በምዘና ስልጠና ላይ

  Return to Top

  ማዕከሉ የጸረ- የኤድስና የጸረ -ሙስና ቀን በዓላትን አከበረ!


  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን"ሁለንተናዊ ልማታችንን እና ሰላማችንን ለማረጋገጥ በሙስና ላይ እንዝመት፣ጊዜው የተግባር ነው"በሚል መሪ ቃል እንዲሁ የኤድስን ቀን"ለኤች አይቪ ኤድስ ይበልጥ ተጋላጭ ነን፣እንመርመር፣ራሳችንን እንወቅ" በሚል መሪ ቃል የማእከሉ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ህዳር 26/2011 በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ በጥምረት ተከብሯል፡፡
  በሀገራችን ለ14ኛ ጊዜ እየታሰበ ያለውን የጸረ ሙስና ቀን አስመልከቶ ሰነድ ያቀረቡት የስነምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ የሆኑት አቶ ቃልኪዳን አድማሴ ሲገልጹ ሙስና እምነት ማጉደልና ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም፣ፍትህን ማዛባት፣የአሰራር ደንብና መመሪያዎችን በመጣስ እንዲሁም በብዙ አይነት መንገድ የሚገለጽ ሲሆን በባህርይው ውስብስብ ጥናትን መሰረት ያደረገ በመሆኑና ጥቅምን ትስስር አድርጎ የሚፈጸም መሆኑ ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚያስከትል እንደሆነ አንስተዋል፡፡በመሆኑም እንደ ተቋም ራሳችንን ቆጥበን የስራ ላይ ስነ-ምግባርን በመላበስ በሌብነት የሚሳተፉ አካላትን በማጋለጥ አጥብቀን ልንዋጋው ይገባል ብለዋል፡፡
  በአለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኤች አይቪ ኤድስ ቀንን አስመልክቶ ሰነድ ያቀረቡት የፕሮጀክት ስልጠናና ማካተት ክፍል ባለሙያ ወ/ሮ ገነት ሀ/እየሱስ ሲገልጹ በሽታው በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ እንደሆነና በተለይም ከ 15-24 ዓመት እድሜ ያላቸውን ወጣቶች እያጠቃ በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶ የመከላከል ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የስርጭት መጠኑ 0.9 የደረሰ ሲሆን በተ.መ.ድ. 2030 በሽታውን ለመግታት እየተሰራ ያለውን ስራ ተቀብላ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አንስተዋል፡፡በመሆኑም ይህንኑ እቅድ ለማሳካት መከላከያ መንገዶችንና አጠቃላይ ስለበሽታው ግንዛቤ በመስጠት ሁላችንም ከራሳችን በመጀመር በየአካባቢያችን የማስተማርና የማስገንዘብ ስራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

       

  የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በኤድስ ስርጭትና በሙስና ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በዕለቱ የጥያቄና መልስ ውድድር ፕሮግራምም ተከናውኗል፡፡

  Latest News:

  ማዕከሉ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አከበረ!


  በአዲስ አበባ ከተማ እስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል 13ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል"በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የማዕከሉ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ህዳር 26/2011ዓ.ም በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ አክብሯል፡፡በዓሉ ህገ-መንግስቱ የጸደቀበትን ቀን ህዳር 29/1987ዓ.ም መሰረት በማድረግ በየዓመቱ በተለያዩ ክልሎች የተከበረ ሲሆን ዘንድሮም በሀገር አቀፍ ደረጃለ 13ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ይከበራል::

  በዕለቱ የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የማዕከሉ ም/ዳይሬክተር አቶ ግደይ ህሽ 13ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ሀገራዊ አንድነት ግንባታን በማጠናከርና በአንድ ሀገር ህዝብ የተለያዩ ክፍሎች መካከል በጋራ ማንነት ወይም ማህበረሰባዊ ስሜትን በመገንባት ላይ መተኮር አለበት ብለዋል፡፡በተጨማሪም ኢትዮጲያ ለህዝቦቿ ምቹና ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል መቻቻል አስፈላጊ እንደሆነና ይህም ሽንፈት ፣ውረደት ወይም ጥቅምን አሳልፎ መስጠት አለመሆኑን ተገንዝበን ከሁሉ በላይ አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶችና የሌሎችን መሰረታዊ ነጻነቶችን እውቅና ከመስጠት የሚመነጭ አወንታዊ አመለካከት መሆኑን አንስተዋል፡፡ሀገራችን ኢትዮጲያ የመቻቻልና አብሮ የመኖር ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን በአሁኑ ሰዓትም እርቅና ሰላም አስፈላጊ ሲሆን ይህም ፖለቲካዊ ምህዳሩን ከማስፋቱም በተጨማሪ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚረዳ ስለሆነ ይህንንም ለማሳካት ከመንግስት ተቋማት ፣ከሚዲያ ፣ከእምነት ተቋማትና አጠቃላይ ማህበረሰቡ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ መወጣት እንደሚገባቸው አስታውሰዋል፡፡

  የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው የዲሞክራሲ ምህዳራችንን ለማስፋት ብዝሀነትን መቀበልና ምክንያታዊ መሆን ብሎም ስለሰላም ስለመቻቻልና እርቅ መስራት አለብን ብለዋል፡፡
  የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀገራችንን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ህዝቦች በጠላትነት መፈረጅ እንደሌለባቸው ፣የዘር ጥላቻ መቆም እንዳለበትና መሰል ተያያዥ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡፡
  በዕለቱ የሻማ ማብራትና ዳቦ ቆረሳ እንዲሁም የጥያቄና መልስ ውድድር ፕሮግራሞች ተከናውነዋል፡፡

   

  Return to Top
  Registerd! Assessed! CertifieD!
  • IMAGES

   Assessment:BAP
    
  • IMAGES

   Assessment:AEE
    
  • IMAGES

   Assessment:SEM
    
  • IMAGES

   Assessment:NUA
    
  • IMAGES

   Assessment:ICT
    
  • IMAGES

   Assessment:ICT
    
  • IMAGES

   Assessment:MAC
    
  • IMAGES

   Assessment:Garment
    
  • IMAGES

   Assessment:BAP
    
   
  Return to Top